የጥበብ ሰዎች መጡ

የጥበብ ሰ−ች መጡ ሰምተውት በዜና
እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና
ሰማይና ምድር የማይወስኑት
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ
አዝ ---
ድንግል እመቤቴ ሰላም ይድረስሽ
ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ
ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድ ን
ኩነኔን አጥፍቶ ክብርን ሊያወርሰን
አዝ ---
ጌ ችን ሲወለድ በቤተልሔም
ኀዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም
እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት
ወንካች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት
አዝ ---
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ
የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ
እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ
እጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ
አዝ ---
← መዝሙር