የጠሩሽ አንቺን ተማጽነው

የጠሩሽ አንቺን ተማጽነው የዳኑብሽ
የበላኤ ሰብእ እመቤት የአምላክ እናት
ድንግል አዛኝት ማርያም ቅድስት
አዝ ----------
በቃል ኪዳንሽ ብዙዎች ድነዋል
በምልጃሽ ጽድቅን አግኝተዋል
የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል
አዝ -----
የእሳት ባሕር በንቺ ተሻግረዋል
ለሰማያዊው ክብር በቅተዋል
አዝ -------
ነፍሳቸውም ጽድቅን አግኝታለች
ሕይወታቸውም በአንቺ ትድናለች
ድንግል ሆይ አትጣይኝ ትላለች
አዝ ----------
እኔም በአንቺ እታመናለሁ
የአምላክ እናት አሳስቢኝ እላለሁ
በአማላጅነትሽ እድናለሁ
አዝ -----------
እኛም በአንቺ እንታመናለን
የአምላክ አሳስቢ እንላለን
በአማላጅነትሽ እንድናለን;2/
አዝ -----------
ምእመናንም በአንቺ ያምናሉ
የአምላክ እናት አሳስቢ ይላሉ
በአማላጅነትሽ ይድናሉ
አዝ ------------
← መዝሙር