የተዘጋች መቅደስ

ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ
የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ
የተዘጋች መቅደስ ንጽሕት አዳራሽ
ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር
ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር
የልዑል ማደሪያ አማናዊት መቅደስ
ስለ ንጽሕናሽ ምስጋናን እናድርስ
አዝ . . .
ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል
ማኅደረ መለኮት ወላዲተ ቃል
ያለ ዘርዓ ብእሲ በኅቱም ድንግልና
አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና
አዝ . . .
ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ
የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሳሺ
ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ
አዝ . . .
← መዝሙር