የፅዮን ልጇ ነኝ
✦
የፅዮን ልጇ ነኝ በአባቶቼ ፋንታ
ስለድንግል ማርያም አልችልም ዝምታ
ፍቅሯን ቀምሻለሁ አልችልም ዝምታ
ስለድንግል ማርያም አልችልም ዝምታ
የቃል ኪዳን ጥላሽ ትውልድ አስጠለለ
አፌ ጠዋት ማታ ብፅዕት ብፅዕት አለ
እንባዬ ደረቀ ጎዶሎዬ ሞላ
ልጅሽ ስላሰበኝ ከቶ ሳይል ችላ
አዝ.................................
ቃል የተፃፈብሽ ንፅዕይት ሰሌዳ
ውዳሴሽ ይቀዳል ከልባችን ጓዳ
ተሰቅሎ ሊያድነን እንዲሁ እኛን ወዶ
እግዚአብሔር መረጠሽ አንቺን ለተዋህዶ
አዝ.................................
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ሞላልኝ ተስፋዬ
እንደ ወራጅ ውሃ አለፈ ስቃዬ
የወለድሽው ፍሬ መርገሜን አፍርሶ
በምስጋና መድረክ አቆመኝ መልሶ
አዝ...................................
እጄን በአፍ የሚያስጭን ክብርሽ ነው ገናና
በእጆችሽ እቅፍ ንጉሱ አለና
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ
ሀናና ኢያቄም የወለዱሽ ፀሀይ
አዝ.................................
‘’ መምህር ምህረተአብ
ስለድንግል ማርያም አልችልም ዝምታ
ፍቅሯን ቀምሻለሁ አልችልም ዝምታ
ስለድንግል ማርያም አልችልም ዝምታ
የቃል ኪዳን ጥላሽ ትውልድ አስጠለለ
አፌ ጠዋት ማታ ብፅዕት ብፅዕት አለ
እንባዬ ደረቀ ጎዶሎዬ ሞላ
ልጅሽ ስላሰበኝ ከቶ ሳይል ችላ
አዝ.................................
ቃል የተፃፈብሽ ንፅዕይት ሰሌዳ
ውዳሴሽ ይቀዳል ከልባችን ጓዳ
ተሰቅሎ ሊያድነን እንዲሁ እኛን ወዶ
እግዚአብሔር መረጠሽ አንቺን ለተዋህዶ
አዝ.................................
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ሞላልኝ ተስፋዬ
እንደ ወራጅ ውሃ አለፈ ስቃዬ
የወለድሽው ፍሬ መርገሜን አፍርሶ
በምስጋና መድረክ አቆመኝ መልሶ
አዝ...................................
እጄን በአፍ የሚያስጭን ክብርሽ ነው ገናና
በእጆችሽ እቅፍ ንጉሱ አለና
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ
ሀናና ኢያቄም የወለዱሽ ፀሀይ
አዝ.................................
‘’ መምህር ምህረተአብ
ዘማሪ መምህር ዘማሪ ዳዊት፣ ለምለም ከበደ
✦