የያሬድ ውብ ዜማ

የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
ምድርና ሰማዩ ታምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ሥራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሽን በዓይኔ አይቻለሁ
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
የእግዚአብሔር ጥበቡ ባንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽ እንድቆም በምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህተና
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ታምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነሽ ስልሽ እጽናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉን አልፈዋለሁ
← መዝሙር