የዘመናት ጌታ
✦
የዕለት የዓመት የዘመናት ጌታ
ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ፪
ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
የሰዉ ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጅመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንደ አንተ አቆጣጠር፪
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንደ አንተ አቆጣጠር፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ስለዚህ አምላክ ሆይ ንዑድ ነዉ ክቡር ነዉ
ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸዉ ሰዉ
ደካማ ነዉና ሰዉ እድሜ ከራበዉ፪
ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸዉ ሰዉ
ደካማ ነዉና ሰዉ እድሜ ከራበዉ፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዮን በኮከብ
እንዳሸበረቀ አስተዉዬ ሳስብ፪
ምድርን በአበባ ሰማዮን በኮከብ
እንዳሸበረቀ አስተዉዬ ሳስብ፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላዉ ዓለምን ብገዛ፪
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላዉ ዓለምን ብገዛ፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ወርኃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ለአንተ ምስጋና እንዲገባ፪
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ለአንተ ምስጋና እንዲገባ፪
ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን
✦