ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ

ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ
አለች የእኛ እናት በትህትና በስጋም በነፍሰም ንፅህይት ናትና
አለች የእኛ እናት በትህትና ድንግል በክልኤ ንፅህይት ናትና
አዝ……………………………………………………………
የአዳም ቃልኪዳን መፈጸሚያው ሲደርስ
ላከው ገብርኤልን ወደ ቤተመቅደስ
በእግዚአብሔር እሊና ተስላ የነበረች
ከሰማይ የመጣ ቃሉን ተቀበለች
ዳግሚት ሰማይ አርያም ሆነች
ይደረግ ብላ በትዕትና ተቀበለች
አዝ……………………………………………………………
ማርያም ሆይ አትፍሪ ብሎ እያረጋጋት
ካንቺ የሚወለደው መድኃኒት ነው አላት
ወንድ ስለማላውቅ ይሄ እንዴት ይሆናል
ብላ ጠየቀችው ድንግልም ደንቋታል
ከሴቶች መሀል አንቺ ልዩነሽ
በህግ ሳይሆን በድንግልና ትፀንሻለሽ
አዝ……………………………………………………………
ሕይወት ቢቀዳባት አድሮኋል በማህጸኗ
አይኖርም ከእንግዲህ የሔዋን መርገሟ
የአዲሱ ኪዳን አዲስ ብስራታችን
ምክንያተ ድህነት አለች እናታችን
ቃልህ ይፈጸም ይደረግ ብላ
ታምር ተሰማ እየሩሳሌም ናዝሬት ገሊላ
አዝ…………………………………………………………
እጅግ አስገረመኝ የገብርኤል ዜና
የነ ዘካርያሰ ከቶ አይደለምና
የተመረጠችው የደረስው ብስራት
አለምን ከመሞት ከመርገሟ ዋጃት
ከሴቶች መሀል አንቺ ልዩነሽ
በህግ ሳይሆን በድንግልና ትፀንሻለሽ
← መዝሙር