ይለፍ ይጠር
✦
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ያቺ የቃየን ድንጋይ የሞት መልእክተኛ
ለማቁሰል ለመግደል ዛሬም አትተኛ
ንጹህ ደም አፍስሰህ አትሁን ቀበዝባዛ
አቤልን አትግደል ቃኤን ልብ ግዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ለማቁሰል ለመግደል ዛሬም አትተኛ
ንጹህ ደም አፍስሰህ አትሁን ቀበዝባዛ
አቤልን አትግደል ቃኤን ልብ ግዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
መተሳሰብ ጠፋ ክፋት ሰለጠነ
እግር ደም ለማፍሰስ አብዝቶ ፈጠነ
መልካም አይታይም መልካም አይሰማ
አምላክ አንተ ሁነን ማምለጫ ከተማ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
እግር ደም ለማፍሰስ አብዝቶ ፈጠነ
መልካም አይታይም መልካም አይሰማ
አምላክ አንተ ሁነን ማምለጫ ከተማ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
አልደራደርም ስላለ በርስቴ
በግፍ ደሙ ቢፈስስ ቢገደል ናቡቴ
አንድ ቀን አይቀርም ዳኛው ፍርድ ይሰጣል
የኤልዛቤልን ደም ውሾች ይልሱታል
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
በግፍ ደሙ ቢፈስስ ቢገደል ናቡቴ
አንድ ቀን አይቀርም ዳኛው ፍርድ ይሰጣል
የኤልዛቤልን ደም ውሾች ይልሱታል
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ጥልና ክርክር በመስቀል ተገድሎ
ይኽው ዛሬ ታይቷል በልባችን በቅሎ
በሥራና በእውነት መዋደድ አብዛልን
እግዚአብሔር አቅልለው የከበደብንንን
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይኽው ዛሬ ታይቷል በልባችን በቅሎ
በሥራና በእውነት መዋደድ አብዛልን
እግዚአብሔር አቅልለው የከበደብንንን
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ለራስ ወዳድነት እጅ የሰጠ ትውልድ
በእሾህ አጥሮበታል የወንድሙን መንገድ
ደግ ሰው አለቀ ፍቅራችን ቀዘቀዛ
እኛ ማለት ቀርቶ እኔን ማለት በዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
በእሾህ አጥሮበታል የወንድሙን መንገድ
ደግ ሰው አለቀ ፍቅራችን ቀዘቀዛ
እኛ ማለት ቀርቶ እኔን ማለት በዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን
በብዙ መከራ ያለንቀት ታመን
✦