ይለመነናል
✦
ይለመነናል አምላክ አብርሐም
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
አብርሐም ይሰሐቅን ያዕቆብን አስበህ
የማልክላቸውን ቃለኪዳን አስታውሰህ
ደካማ ለሆነው ሥጋ ስልጥኖብን
አትመለስ ጌታ የምህረት ዓይንህን
ከሰማየ ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን
እንዘን እናልቅስ ስለ በደላችን፪
የማልክላቸውን ቃለኪዳን አስታውሰህ
ደካማ ለሆነው ሥጋ ስልጥኖብን
አትመለስ ጌታ የምህረት ዓይንህን
ከሰማየ ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን
እንዘን እናልቅስ ስለ በደላችን፪
ይለመነናል አምላክ አብርሐም
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ባይመለከተን አምላከ አብርሐም
በምሕረት ዓይኖቹ መድሃኔዓለም
ባይዘረጋልን አምላከ አብርሐም
የፍቅር እጆቹን መድኃኔዓለም
ሕዝበ እሰራኤል ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ
አደኖናልና በሚያስደንቅ ፍቅሩ፪
በምሕረት ዓይኖቹ መድሃኔዓለም
ባይዘረጋልን አምላከ አብርሐም
የፍቅር እጆቹን መድኃኔዓለም
ሕዝበ እሰራኤል ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ
አደኖናልና በሚያስደንቅ ፍቅሩ፪
ይለመነናል አምላክ አብርሐም
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ምንም እንኳን ክህደት ቅጥፈት ቢበረታ
ስለ አብርሐም ብለህ አልተወከንም ጌታ
ለቅዱሳን ያለህ ቃል ኪዳን ሲጸና
ቀስተ ደመናህን አይተነዋልና
የእሰራኤል አምላክ የማታንቀላፋ
በፍቅርህ ታደገን በሞት ሳንጠፋ፪
ስለ አብርሐም ብለህ አልተወከንም ጌታ
ለቅዱሳን ያለህ ቃል ኪዳን ሲጸና
ቀስተ ደመናህን አይተነዋልና
የእሰራኤል አምላክ የማታንቀላፋ
በፍቅርህ ታደገን በሞት ሳንጠፋ፪
ይለመነናል አምላክ አብርሐም
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ይታደገናል መድሃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ፪
ቃልዳኑ ግሩም አምላከ አብርሐም
ምሕረቱ የበዛ መድኃኔዓለም
ርስት ጉልታችን አምላከ አብርሐም
የህይወታችን ቤዛ መድኃኔዓለም
ሳይጸየፍ ጌታ ያደፈ ኃጢአቴን
ከማጥ ውስጥ አወጣኝ ታደጋት ሕይወቴን፪
ምሕረቱ የበዛ መድኃኔዓለም
ርስት ጉልታችን አምላከ አብርሐም
የህይወታችን ቤዛ መድኃኔዓለም
ሳይጸየፍ ጌታ ያደፈ ኃጢአቴን
ከማጥ ውስጥ አወጣኝ ታደጋት ሕይወቴን፪
✦