ይትባረክ እንደ አብርሃም

ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
የአካል አንድነት---- እንደ አብርሃም
በቁርባን ተሳስሮአል ----- እንደ አብርሃም
ከዛሬ ጀምሮ ---------- እንደ አብርሃም
ሁለትነት ጠፍቷል ------ እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
ከአካሉ ተጣብቃ ---- እንደ አብርሃም
ዘመናት የኖረች ----- እንደ አብርሃም
ዘመረች በደስታ ----- እንደ አብርሃም
አካሏን አገኘች ----- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
ቡሩክ ነው ምንጣፉ---- እንደ አብርሃም
ጸጋ የከበበው ------ እንደ አብርሃም
የሙሽሮች ድንኳን --- እንደ አብርሃም
አምላክ ያልተለየው --- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
እልል በሉላቸው ----- እንደ አብርሃም
ዛሬ ነው ሠርጋቸው --- እንደ አብርሃም
የተመረጡበት ------- እንደ አብርሃም
መልካም ጋብቻቸው --- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
ድንግል ሆይ ባርኪልን ሙሽሮቹን
ባርኪልን
የሙሽራው መልካም ፍሬ
የሙሽሪት መልካም ፍሬ
አምራ ደምቃ ታየች ዛሬ
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
ከአዳም አንድ አጥንት---- እንደ አብርሃም
ከጎኑ ወስደህ --------- እንደ አብርሃም
አጋር እንድትሆነው ----- እንደ አብርሃም
ሔዋንን ሰጠህ -------- እንደ አብርሃም
ሁለቱንም ባርከህ ------ እንደ አብርሃም
እንደፈጠርካቸው ------ እንደ አብርሃም
ዛሬም ለሙሽሮች ------ እንደ አብርሃም
ሰላምን ስጣቸው ------- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
መተሳሰብ ይኑር --- እንደ አብርሃም
በመካከላችሁ ----- እንደ አብርሃም
ሠርጎ እንዳይገባ --- እንደ አብርሃም
ሰይጣን ጠላታችሁ --- እንደ አብርሃም
በፆም እና ጸሎት --- እንደ አብርሃም
ይታጠር ጓዳችሁ --- እንደ አብርሃም
ድንግል እየመጣች --- እንደ አብርሃም
እንድትባርካችሁ --- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
በቃልህ ተመርተው---- እንደ አብርሃም
ለዚህ ቀን ደርሰዋል --- እንደ አብርሃም
በፊትህ ጋብቻን ------ እንደ አብርሃም
ይኸው ፈጽመዋል ----- እንደ አብርሃም
በፈሰሰው ደምህ ----- እንደ አብርሃም
ሕብረት መስርተዋል --- እንደ አብርሃም
በሥጋም በነፍስም
ያንተ ነን ብለዋል
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
ጌታ ሆይ በህግህ---- እንደ አብርሃም
በቃልህ መሠረት --- እንደ አብርሃም
አንድ ሆነዋልና ---- እንደ አብርሃም
በዚች ቅድስት ዕለት - እንደ አብርሃም
እርሱንም እርሷንም -- እንደ አብርሃም
ባርክህ ቀድሳቸው --- እንደ አብርሃም
ዘለዓለማዊ ክብር --- እንደ አብርሃም
ጸጋህን ስጣቸው ---- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
የዲያብሎስ ተንኮል---- እንደ አብርሃም
እንዳያጠምዳቸው ---- እንደ አብርሃም
እመቤቴ ማርያም ----- እንደ አብርሃም
ከለላ ሁኛቸው ------- እንደ አብርሃም
ከዚህች ቅድስት ቤት --- እንደ አብርሃም
ሁለቱም ሳይርቁ ------ እንደ አብርሃም
ፅናቱን ይስጣቸው ----- እንደ አብርሃም
አብረው እንዲዘልቁ ---- እንደ አብርሃም
ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ
ዘለዓለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
← መዝሙር