ዮሐንስን ይዛ

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ስለ ልጇ ሐዘን ስለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰ እንባዋ
ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ፅናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያፅናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እህት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን
የማርያም ሐዘን
አዝ=====
መግደላዊት ማርያም ሰሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ፀንቶባት ሃዘኗ
በለቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
እንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን
የማርያም ሐዘን
አዝ========
ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያቆብም አልቅሷል በሌላ የሰው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን
የማርያም ሐዘን
አዝ========
ጠብቶ ስላደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሽፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከስጋዋ ነብሷን
← መዝሙር