ዮም ፍሥሐ ኮነ
✦
ኃጢአት በዓለም ነግሣ
በድንግል መወለድ
ቀረልን አበሣ
እግዚአብሔር መረጠሸ
ልትሆኚ እናቱ
ይኸው ተፈጸመ
የዳዊት ትንቢቱ
አዝ ---
የሔዋን ተስፋዋ
የአዳም ሕይወት
የኢያቄም የሐና
ፍሬ በረከት
ምክንያተ ድኅነት
ኪዳነምሕረት
ድንግል ተወለደች
የአምላክ እናት
አዝ ---
በሔዋን ምክንያት
ያጣነውን ሰላም
ዛሬ አገኘነው
በድንግል ማርያም
የምሥራች እንበል
ሐዘናችን ይጥፋ
ተወልዳለችና
የዓለም ሁሉ ተስፋ
አዝ ---
በድንግል መወለድ
ቀረልን አበሣ
እግዚአብሔር መረጠሸ
ልትሆኚ እናቱ
ይኸው ተፈጸመ
የዳዊት ትንቢቱ
አዝ ---
የሔዋን ተስፋዋ
የአዳም ሕይወት
የኢያቄም የሐና
ፍሬ በረከት
ምክንያተ ድኅነት
ኪዳነምሕረት
ድንግል ተወለደች
የአምላክ እናት
አዝ ---
በሔዋን ምክንያት
ያጣነውን ሰላም
ዛሬ አገኘነው
በድንግል ማርያም
የምሥራች እንበል
ሐዘናችን ይጥፋ
ተወልዳለችና
የዓለም ሁሉ ተስፋ
አዝ ---
✦