ዘጠኝ ሠዓት ሲሆን

ዘጠኝ ሠዓት ሲሆን ጌታ ሆይ በመስቀል ሆነህ ጌታ ሆይ
ድምፅን በማሰማት ጌታ ሆይ ነፍስህን ሰጠህ ጌታ ሆይ
የሰማይ ከዋክብት በሙሉ አዘኑ
ጨረቃና ፀሐይ ምስክሮች ሆኑ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህ በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ቅመሰው ብለው
ቀኝ ጎኑ ሲወጋ ውሃና ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለሙን ቀደሰ
የእስራኤል ልጆች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለራስህ አላሰብህ
እናትህ ስታለቅስ በመስቀል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጠሃት ጠብቆ እንዲጽናና
መላእክት ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ
ዘማሪ በየነ ድንቁ፣ ዜማ ኪነ ጥበብ
← መዝሙር