ዘይክል ኲሎ

ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር
አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን
ንኅነ ሀቤከ ተማፀነ
የድሆች አለኝታ ተስፋ ላጡ ተስፋ
ሁሉንም የሚችል ደራሽ ለተገፋ
ለእኛም ድረስልን በኃጢአት ሳንጠፋ
አዝ . . . /ናዛዜ ኅዙናን/
ከገነት ሲባረር አዳም ተሳስቶ
ባለቀሰ ጊዜ ልጅነቱን አጥቶ
ትድናለህ ብለህ ያዳንከው በመስቀል
የቅዱሳን አምላክ አቤቱ ቸል አትበል
አዝ . . . /ወተስፋ ቅቡጻን/
ሕዝበ እስራኤልን ፈርኦን ሲገዛቸው
ጭንቅና መከራ እያጸናባቸው
በእነራሔል ልቅሶ ሙሴን ላክህላቸው
አዝ . . . /ረዳኤ ምንዱባን/
እኛም ወገኖችህ ወደ አንተ እንጮሃለን
ከጭንቅ ከመከራ እንድትታደገን
ጌታ አንተ ነህና ናዛዜ ኅዙናን
አዝ . . . /ናዛዜ ኅዙናን/
አዝ . . . /ወተስፋ ቅቡጻን/
← መዝሙር