ዝም አትበሉ

ዝም አትበሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቅዱስ በሉ
መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱሰ በሉ
የሙሴ እኅት ማርያም ከበሮውን አንሺው
በምሥጋና መዝሙር እሥራኤልን ጥሪው
አምላክን እናክብር እንዘምር በእልልታ
ከእኛ ጋር ይሆናል የሠራዊት ጌታ
ዝም አትበሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቅዱስ በሉ
መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱሰ በሉ
ፍጥረታትም ጩኹ ሰማያት ዘምሩ
ስለቅድስናው ሁላችሁ ዘምሩ
ዳዊት ሆይ ተነሣ ስለ ጽዮን ዘምር
ከበሮው ይመታ በገናው ይደርደር
ዝም አትበሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቅዱስ በሉ
መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱሰ በሉ
ወገኖች እንዘምር ለእግዚአብሔር ክብር
ውለታው ብዙ ነው ለእኛ ያለው ፍቅር
ማዳኑን ያያችሁ ዘምሩ በእልልታ
ለጌታ ለእግዚአብሔር ለሠራዊት ጌታ
ዝም አትበሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቅዱስ በሉ
መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱሰ በሉ
ባሕሩን አቋርጦ ወንዝ ያሻገራችሁ
ተራራውን ንዶ አቀለለላችሁ
በአውሎ ነፋስ መሃል መንገድ አለው ጌታ
ለንጉሥ ክርስቶስ እንዘምር በእልልታ
ዝም አትበሉ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቅዱስ በሉ
መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱሰ በሉ
← መዝሙር