ዝናማትም ዘነሙ

ዝናማትም ዘነሙ ወንዞችም ጎረፉ
የአምላክን ጸጋ እያትረፈረፉ
ሰማያትም ዘመሩ በልዑል ቃሉ
የፍጥረታት ሁሉ መጋቢ አንተ ነህ እያሉ
ገበሬውም አረሰ ፈጣሪውን አምኖ
ዘርንም በተነ በምድር ላይ ከጎተራው ዘግኖ
ደመናትም ዓለምን ይዞራሉ
በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ዝናምን ሊያድሉ
በልምላሜ ተዋቡ ዕፅዋት አዝርእቱ
ፍሬን ይሰጡ ዘንድ አብዝተው በጊዜው በወቅቱ
መሬትም ለአራሿ አድርጋ ውለታ
የላቡን የወዙን ከፈለች እንዳዘዘ ጌታ
ድካሙን ጥረቱን አምላክ ተመልክቶ
አንዷን ፍሬ ሰጠው አብዝቶ አድርጎ መቶ
ዝናምንም ለዘር ልምላሜን ለፍሬ
የሰጠን አምላክ ይመስገን ይክበር በዝማሬ
← መዝሙር