በ 2008 አም የ ስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ የአማርኛ መምህራችን እናት አለም ወርቁ ትባል ነበር ። የምወዳትና የማከብራት መምህሬ። ወደዋናዉ አላማዬ ስገባላችሁ እካ ስላንትያ ግጠሙ ባለችን ወቅት የሚከተለዉን እንካ ስላንትያ አዘጋጅቼ አቀረብሁ።

(መልካም ምንባብ)
እንካ ስላንትያ በምንትያ
በፓፓያ ምናለ በፓፓያ?
ጎበዝ ተማሪ ነዉ መሪዉ ለ ኢትዮጵያ
እንካ ስላንትያ በምንትያ፥
በትንኝ ምናለ በትንኝ?
ጎበዝ ህዝባችን ነዉ እኔን ደስ የሚለኝ።
እንደዚህ አርግ እንጂ እያለ ሲያስረዳኝ።
እንካ ስላንትያ በምንትያ
በበሽታ ምናለ በበሽታ?
መኖር ከጀግናዉ ህዝብ ይሰጠኛል ፋታ
ማስታወሻነቱ በወቅቱ የ አማርኛ መምህሬ ለነበረችው መምህርት እናት አለም ወርቁ
እሱባለው