በ 2008 ዓ.ም. የ ስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፤ የአማርኛ መምህራችን እናት ዓለም ወርቁ ትባል ነበር ። የምወዳትና የማከብራት መምህሬ። ወደ ዋናው አላማዬ ስገባላችሁ እንካ ስላንቲያ ግጠሙ ባለችን ወቅት የሚከተለውን እንካ ስላንቲያ አዘጋጅቼ አቀረብሁ።
(መልካም ምንባብ)
እንካ ስላንቲያ በምንትያ
በፓፓያ ምናለ በፓፓያ?
በፓፓያ ምናለ በፓፓያ?
ጎበዝ ተማሪ ነው መሪው ለ ኢትዮጵያ፤
እንካ ስላንቲያ በምንትያ፥
እንካ ስላንቲያ በምንትያ፥
በትንኝ ምናለ በትንኝ?
ጎበዝ ህዝባችን ነው እኔን ደስ የሚለኝ።
እንደዚህ አርግ እንጂ እያለ ሲያስረዳኝ።
እንደዚህ አርግ እንጂ እያለ ሲያስረዳኝ።
እንካ ስላንቲያ በምንትያ
በበሽታ ምናለ በበሽታ?
መኖር ከጀግናው ህዝብ ይሰጠኛል ፋታ
በበሽታ ምናለ በበሽታ?
መኖር ከጀግናው ህዝብ ይሰጠኛል ፋታ
ማስታወሻነቱ በወቅቱ የ አማርኛ መምህሬ ለነበረችው መምህርት እናት ዓለም ወርቁ
እሱባለው